ኤቲካል ኤአይ /Annotate plus

EthicalAI /Annotate Plus ከፍተኛ አቅም ያለው የዳታ መለያ እና መተንተኛ ፕላትፎርም ሲሆን፤ የAI ሞዴሎችን ለሚገነቡ የተለያዩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ፍትሃዊ ፣ ትክክለኛነት እና ውጤታማ የAI ሞዴሎችን እንዲገነቡ የሚያግዝ መድረክ ነው፡፡
በግልጽነት፣ በትክክለኛነት እና በሥነ-ምግባራዊ መርሆዎች ላይ በማተኮር፣ የተለያዩ ምስሎች፣ ቪዲዮዎች፣ ድምጽ፣ ጽሑፍ እና 3D የዳታ ስብስቦችን በመጠቀም EthicalAI /Annotate Plus አስተማማኝ የኤአይ ውጤቶችን ለመገንባት ያግዛል።
ፕላትፎርሙ በሚጠቀመው ዳታ ላይ ትልቅ የጥራት ቁጥጥር የሚያረግ ሲሆን፣ በተፈለገ ጊዜ በቦታ ሄዶ ዳታን በመሰብሰብ እንዲሁም የተመረጡ ታማኝ ምንጮችን በመጠቀም ጥራት ያላቸው ዳታዎችን ለትንተና ስራ ያውላል፡፡

 

What You Will Learn

  • ለኤአይ ፕሮጀክቶች የተለያዩ የዳታ አይነቶችን (ምስል፣ ቪዲዮ፣ ድምፅ፣ ጽሑፍ፣ 3D) መለያ እንዴት ማድግ
    እንደሚችሉ (annotation)
  • ዳታ ምልክት ማድረጊያ (data labeling) ላይ ትክክለኛነት፣ ጥራት እና ሥነ-ምግባራዊ ደረጃዎችን ለመጠበቅ
    ምርጥ ተሞክሮዎችን ማሳወቅ
  • ዓለም አቀፍ የኤአይ እድገትን ለመደገፍ የጋራ የሥራ ፍሰት (collaborative workflows) እንዴት
    እንደሚጠቀሙ።
  • በሥነ-ምግባር የተገኘ ዳታ ተጠያቂ እና ሁሉን አቀፍ የኤአይ መፍትሄዎችን በማምጣት ውስጥ ያለው ሚና።

Who is this Program For

  • ተስማሚ በሆኑ ሰዓቶች እና ቦታዎች ላይ የዲጂታል ስራ መስራት የሚፈልጉ ወጣቶች
  • ለዓለም አቀፍ የኤአይ ፕሮጀክቶች አስተዋፅዖ ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች።
  • አስተማማኝ እና በሥነ-ምግባር የተገኘ የዳታ መለያ ማድረጊያ አገልግሎት (data annotation services)
    ለማግኘት የሚፈልጉ ድርጅቶች እና አዳዲስ ተቋማት (startups)።
  • Disadvantage groups ከስደት ተመላሾች፣ አካል ጉዳተኞች እና በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች

Program Outcome

በEthicalAI / Annotate Plus በመሳተፍ ዳታዎችን ትንተና እና መለየ ስራ ላይ የስራ ላይ ልምድ ያገኛሉ፤
በተመሳሳይ ጊዜ በዲጂታል እና ጊግ ኢኮኖሚ ውስጥ ለመስራት አስፈላጊ የሆኑትን መሰረታዊ ክህሎቶች (soft skills)
ያጠናክራሉ። ፕሮግራሙ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተስማሚ በሆኑ ሰዓቶች እና ቦታዎች ሊሰሩ የሚችሉ የዲጂታል
የሥራ እድሎችን በማገናኘት የተለያዩ የኤአይ ቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶች ስራ ላይ በመሳተፍ ለኤአይ እድገት አስተዋፅዖ
እንዲደርጉ ያጠናክርዎታል።

Related Products

ቅኝት
ሃይብሪድ ዲዛይንስ
ቅኝት
በውድድር የሚመራ የገበያ ቦታ ብራንዶችን ከፈጠራ የጊግ ሰራተኞች ጋር የሚያገናኝ፣ ፈጣሪዎች የሚሸጡበት፣ የሚሸጡበት እና የሚታወቁበት፤ ከሚከፈልባቸው የሽምግልና ሚናዎች ጋር ተጣምሯል. Qegnet የአገር ውስጥ ፈጠራን ወደ ንግድ ሥራ፣ ሽልማቶች እና ለዲዛይነሮች እና የእጅ ባለሞያዎች ተደጋጋሚ ኮሚሽኖችን ይለውጣል።
ፈጥሮ አደር
ሃይብሪድ ዲዛይንስ
ፈጥሮ አደር
የችርቻሮ ገቢር እና የተቆራኘ መድረክ ንግዶችን ከአካባቢያዊ የጊግ ሰራተኞች ጋር የሚዛመድ ለላይ እና ከመስመር ውጭ ለሚሰሩ ማይክሮ ስራዎች እና የዲጂታል ስራን ገቢ ለመፍጠር የሚያስችል የንብረት መያዣ። የተለያዩ የገቢ ዥረቶችን ያጠቃልላል ስለዚህ gig ሰራተኞች ከተግባሮች፣ ከዲጂታል ንብረቶች እና ከሽያጮች ገቢ ያገኛሉ።
ኤቲካል ኤአይ /Annotate plus
R & D Group
ኤቲካል ኤአይ /Annotate plus Type / to choose a block
ወጣቶችን በምስል፣ ቪዲዮ፣ ጽሑፍ፣ ድምፅ እና 3D ዳታዎችን ትንተና እና መለየት ስራ ላይ በማብቃት የዓለም አቀፍ የAI ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሳተፉ የሚያግዝ ትልቅ ፕላትፎርም ነው። EthicalAI /Annotate Plus በጥራት የተጠበቁ የዳታ ስብስቦችን ሲያቀርብ፣ ለወጣቶች በተለይም ለወጣት ሴቶች ፣ አሳታፊ፣ ተስማሚ በሆኑ ሰዓቶች እና ቦታዎች ሊሰሩ ሚችሉ የዲጂታል የሥራ እድሎችን ይፈጥራል።